OUR STATE
OUR LANGUAGES

ተቀላቀለን

በቴንሲ ነዋሪዎችና የንግድ ባለቤቶች እንደመሆናችን ስቴቷ የነዋሪዎቿን ቋንቋ በቀላሉ የምታቀርብና የምታንጸባርቅ እንድትሆን እንጠይቃለን።

የእኛ ስቴት የእኛ ቋንቋዎች የሚለውን ህብረት ጋር ሆናችሁ ቴነሲን ወደፊት ማስኬድ የሚለው መርሆ እንዲሰራ የመኪና መንጃ ፈቃድ በቋንቋችን እንዲቀርብ ብላችሁ አስታውቁ።  

የመንጃ ፈቃድ አለመኖር ለንግድ ስራ፣ ለሰራተኞች፣ ለልጆችና ለህዝብ ደህንነት ትልቅ ሸክም ነው የሚሆነው። ይሄ ጉዳይ ትናንንሽ የንግድ ስራዎች ላይና ኢኮኖሚያችን ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል በተለይም በአሁኑ ጊዜ የሰራተኞች እጥረት ባለበት። ይሄ መሆኑ በስቴቱ ውስጥ ዋጋዎችን ከፍ የማድረግ አስተዋጽኦ ይኖራል። ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ሐኪም ጋ መውሰድ ሲያቅታቸው ጭንቀት ነው። ኑሮን ለማሸነፍ ሲሉ ሰዎች ህጋዊ የመንጃ ፈቃድ ሳይኖራቸው ሲነዱ ደህንነታችን አደጋ ላይ ይወድቃል። ሰዎች በኑሮ እድገት ለማግኘት የስራ  እድል ሲያመልጣቸው ለምሳሌ የጭነት መኪና ነጂ ለመሆን፣ የመላኪያ ሹፌርና የታክሲ ነጂ ለመሆን ስቴቱ ወደኋላ የቀሩ ፖለሲዎችን በመጠቀም መንገዱን ሳይከፍትላቸው ሲቀር በኢኮኖሚ ማደግም አይኖርም።  

Members